የኮልሜ ወረዳ በኮንሶ ዞን ከሚገኙ 4 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ወረዳዉ በ 5016’15” እስከ 5021′20′′ ሰሜን ላቲትዩድ እና በ 37020′ 15′′ እና 37026’49′′ ምሥራቅ ሎንግትዩድ መሥመሮች ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን አዋሳኞቹ በደቡብ የቦራና ዞን (ቴልቴሌ ወረዳ)፣ በምዕራብ የደቡብ ኦሞ ዞን (በና ፀማይ ወረዳ)፣ በሰሜን የኧሌ ዞን (ኮላንጎ ዙሪያ ወረዳ) እንዲሁም በምሥራቅ ከና ወረዳ እና ካራት ዙሪያ ወረዳ ናቸዉ፡፡ ወረዳዉ ከባህር ጠለል በላይ ከ501—2000 ሜትር ከፍታ ያላቸዉን ሥፍራዎች የሚሸፍን ሲሆን አየር ንብረቱም 70% ደረቅ ቆላማ፣ 30% ደግሞ ወይና ደጋ እንደሆነና ዓመታዊ አማካይ የሙቀቱ መጠን ከ 17.8 ዲግር ሴንትግሬድ እስከ 28.6 ይደርሳል፡፡ የወረዳዉ ቆዳ ስፋት 454.3 ኪ.ሜ2ሲሆን ፡፡ የሕዝብ ሥርጭት/አሰፋፈር/ ከቦታ ቦታ የሚለያይ ሲሆን ጥግግቱ በስኩየር ኪ.ሜትር 106 ሰው ነው፡


