የተቋማት ግንባታ

የተቋም ግንባታ መሠረታውያን

መግቢያ

የምንገኝበት ዘመን በጣም ፈጣንና ተለዋዋጭ ነው። በየጊዜው አዳዲስ ችግሮችን እናስተናግዳለን። የሥራ ጫናው ካለው የሠራተኛ ብዛት አንጻር ሲታይ የት የለሌ ነው። ከላይኛው የመንግሥት መዋቅር የሚወርዱ ተልእኮዎች ሁሉ የሚራገፉት የወረዳ አመራር ላይ ነው። የወረዳ አመራር ተልዕኮውን ተቀብሎ ወደ ቀበሌ ያወርዳል። ወረዳ ላይ ያሉ አመራሮችና ሠራተኞ በተራቸው የተሰጣቸውን ተልእኮ ፈጽመው ርፖርቱን ለወረዳ አመራር እንዲያስረክቡ ይፈለጋል። ሆኖም ግን እንደ ወረዳችን መንግሥታዊ አሠራር የቆየ ታሪክ ቢኖረውም በሙሉ ዐቅሙ ወደ ሕዝብ ወርዶ ሁሉንም ተግባራት ማከናወን የጀመረው ገና ወረዳው ሲቋቋም ነው። በዚህ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጡ ተልእኮዎች በብዙ ድጋፍና ውትወታ ካልሆነ በስተቀር አፈጻጸማቸው እየተንገዳገደ ያስቸግራል። ለዚህ ዋንኛ ምክንያቱ ደግሞ ተቋማት ባለመፈጠራቸው ነው። በየቀበሌ ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ ተቋማት በሥርዐት ስላልተደራጁ ዛሬም ኀላፊነታቸውን በወጒ የማይገነዘቡ፣ በቂ ሀብት የሌላቸው፣ የሚሠሩበትን ዓላማ ያልገባቸው ሠራተኞች የያዙ ተቋማት ሆነው ቆይተዋል። ይኸ ሁኔታ በወረዳ ደረጃ bበሚሠሩ የአመራሮች ላይ ከፍተኛ የሥራ ጫና እያሳደረ ይገኛል። በዚህ ምክንያት ችግሮች በሂደት እየተቀረፉ፣ ሥራዎች ያለ ብዙ ድጋፍና ያለ ብዙ የሰው ኀይል በራሳቸው በሚመለከታቸው ሠራተኞች ብቻ መከናወን እንዲችሉ ሁሉም አማራሮች ተቋማዊ አሠራሮችን እንዲዘረጒ ያስፈልጋል። ከዕለታዊ ተግባሮቻቸው ጎን ለጎን የተቋም ግንባታ እንዲያካሂዱ ከወዲሁ እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ያስፈልጋል።

ትርጉሞች

የተቋም ግንባታ ከማየታችን በፊት ድርጅት (organization)ና ተቋም የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ትንሽ ግልጽነት መፍጠር አስፈላጊ ነው።

ድርጅት (organization) ድርጅት ማለት ግልጽ በሆነ መዋቅር ተደራጅተው ለጋራ ዓላማ የሚሠሩ የሰዎች ሰብስብ ነው። በዚህ አጠር ባለ ትርጉም ውስጥ የተቀመጡ ቃላት መረዳት ሐሳቡን ግልጽ ያደርገዋል።

  • ግብ፦ ሰዎቹ የተሰባሰቡበት አንድ የጋራ ዓላማ ወይም ግብ ያሰፈልጋቸዋል። ግብ ድርጅቱ ለምን እንደተቋቋመ ምላሽ የሚሰጥ ነው። ስለዚህ የድርጅት ቀዳሚ ተግባር ከሆኑት መካከል አንዱ ግብ ማስቀመጥ ነው።
  • መዋቅር (Structure):– የተሰባሰብ ሰዎች በዘፈቀደ የሚሠሩ ሳይሆን ኀላፊነት ተከፋፍሎላቸው በራሳቸው ማዕቀፍ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ አንዱ የድርጅት ዋና ሐሳብ ነው። በሰዎች መካለ የኀላፊነትና
  • ሰዎች፡ የተጣለውን ግብ የሚፈጽሙ ሠራተኞች ናቸው። የድርጅቱ ባለቤቶች፣ ኀላፊዎችና መደበኛ ሠራተኞችን ያጠቃልላል። ብዙውን ጊዜ ድርጅቱ በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች ባለቤትነት ሊተዳደር ይችላል። ወይም በመንግሥት ሊተዳደር ይችላል።

ለምሳሌ፡ ት/ቤት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ቴሌ፣ ጉግል፣ ወዘተ. . . ድርጅቶች ናቸው።

ተቋም(Institution) ሰፋ ያለ ሐሳብና እንደየ አውዱ የተለያዩ ትርጒሞችን የያዘ ቃል ነው። በጥቅሉ ሲታይ ግን ተቋም ድርጅት ላይ ተጨማሪ እሴቶች ሲጨመሩበት የሚፈጠር የኀላፊነት አካል ነው። በአጭሩ ተቋምን እንዲህ መግለጽ ይቻላል። በተቋቋመ ድርጅት ላይ እሴቶች ሲጨመሩ የምናገኘው ማኅበራዊ አካል ነው። 

ተቋም = ድርጅት + እሴቶች

እሴት

 እሴቶች የምንላቸው ነገሮች ባህል፣ ልማዶች፣ የአሠራር ሥርዐቶች፣ ልምምዶች፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባሮች (professional ethics) ወዘተ ሊያጠቃልል ይችላል። እሴቶች የተቋሙን ባህሪይ፣ የውሳኔ አሰጣት ሂደት፣ ባህልና ማንነት የምንጸባርቅባቸው እምነቶችና መርሆች ናቸው። ከሕጎችና ደንቦች የበለጠ የተቋሙን ማንነት የሚመራው የተቋሙ እሴት ነው።

አንድ ድርጅት ለማኅበረሰብ አንዳች የሚረባ አስተዋጾኦ የሚያበረክት ከሆነ ተቋም ይሆናል። ተቋም የድርጅት የአሠራር ሥርዐት (System) ሊሆን ይችላል። ብዙውን ጊዜ ድርጅት በዓይን የሚታይ፣ በእጅ የሚጨበጥ ቁሳዊ ነገሮችን የሚወክል ሲሆን ተቋም ደግሞ የማይጨበጡ ነገሮችን ይይዛል። ለምሳሌ ሕንጻ፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሰዎች፣ በጀት፣ ወዘተ. . . የድርጅት አካላት ሲሆኑ፣ የአሠራር ሥርዐቶች፣ የድርጅቱ ባህል (organizational culture), ወጎች (norms), ፖሊሲዎች፣ ሕጎች ወዘተ. . . የያዘው ክፍል ተቋም ይሆናል። ተቋም ባህሪይን (behavior) ያስተዳደራል, ይመራል። ተቋማት የብዙ ድርጅቶች ድምር ውጤቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ት/ቤት ድርጅት ሲሆን የትምህርት ተቋማት ሲባል ግን በአንድ አገር ውስጥ ያሉ ት/ቤቶች በሙሉ የሚተዳደሩበት ሥርዐትን ሊያመለክት ይችላል። ለምሳሌ የ1ኛ ወይም 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ዪኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች በአንድነት የትምርህት ተቋማት ሊባሉ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲባል ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም የመንግሥትና የግል ዪኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችን የሚያካትት ነው። የጤና ተቋማትም በተመሳሳይ መልኲ የብዙ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎችና ጤና ኬላዎች ድምር ውጤት ሊሆን ይችላል። ድርጅቶች የሕይወት ዑደት አላቸው፣ ይወለዳሉ (birth)፣ ያድጋሉ (growth)፣ ይጎለምሳሉ(maturity)፣ ያረጃሉ(decline)። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ሳያረጁ ለረጅም ጊዜ የመቆየት ዐቅም ከፈጠሩ ወደ ተቋም ደረጃ ያድጋሉ። ተቋም በጊዜ ርዝማኔ የሚፈጠር ሥርዐት ነው። ገና በውልደት ደረጃ ካለ ድርጅት እንጂ ተቋም ሊሆን አይችልም። ተቋማት ጠንካራ ሥርዐቶችና ደንቦች ስላሏቸው በሰዎች መቀያየር አይቀየሩም። ዘመናትን ዘልቀው ይሄዳሉ። ድርጅቶች ግን ጊዜያዊ ናቸው፣ ምናልባት የተቋቋሙበት ዓላማ ሲጨርሱ ሊከስሙ ይችላሉ፣ አሊያም በጊዜ ርዝማኔ ተፈትነው ሊወድቊ ይችላሉ።

ይቀጥላል

  • Related Posts

    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፫)

    የተቋም ግንባታ ሥራዎች አገራችን ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዐተ መንግሥት ቅርጽ የምትከተል በመሆኗ መዋቅራዊ አደረጃጀቱ ተዋረዳዊ (Hierarchical) ነው። ተዋረዱ ከላይ ወደ ታች ሲዘረዘር ፈዴራል፣ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ ናቸው። ሥልጣንና ተግባራት…

    ማንበብ ይቀጥሉ

    Continue reading
    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፪)

    የተቋማት ግንባታ ምንነት ድርጅቶች ወደ ተቋም ደረጃ አድገው ዘመናትን ተሻግረው በማኅበረሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ አካል መሆኑ እንዲችሉ በተጠና መንገድ መገንባት አለባቸው። የተቋማት ግንባት የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። ከዘመን ጋር አብረው የሚቀየሩ…

    ማንበብ ይቀጥሉ

    Continue reading

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *

    You Missed

    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፫)

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 131 views
    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፫)

    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፪)

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 113 views
    የተቋማት ግንባታ (ክፍል ፪)

    የተቋማት ግንባታ

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 94 views
    የተቋማት ግንባታ

    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፫)

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 79 views
    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፫)

    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፪)

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 133 views
    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፪)

    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፩)

    • By admin
    • June 27, 2026
    • 88 views
    የሰላም ግንባታ (ክፍል ፩)