የኮልሜ ወረዳ በኮንሶ ዞን ውስጥ ካሉ አራት ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን መልክዐ ምድራዊ አቀማመጡ በ5016’15” እስከ በ5021′20′′ ሰሜን ላቲትዩድ እና በ 37020′ 15′′ እና 37026’49′′ ምስራቅ ሎንጊትዩድ መሥመሮች ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን አዋሳኞቹ በደቡብ የቦራና ዞን(ቴልቴሌ ወረዳ)፣በምዕራብ የደቡብ ኦሞ ዞን (በና ፀማይ ወረዳ)፣ በሰሜን የኧሌ ዞን(ኮላንጎ ዙሪያ ወረዳ) እንዲሁም በምስራቅ ከና ወረዳ እና ካራት ዙሪያ ወረዳ ናቸዉ፡፡ ወረዳዉ ከባህር ጠለል በላይ ከ501—2000 ሜትር ከፍታ ያላቸዉን ሥፍራዎች የሚሸፍኑት ሲሆን አየር ንብረቱም 70% ደረቅ ቆላማ፣ 30% ደግሞ ወይና ደጋ እንደሆነና አመታዊ አማካይ የሙቀቱ መጠን ከ17.8 ዲግር ሴንትግሬድ እስከ 28.6 ይደርሳል፡፡ የወረዳዉ ቆዳ ስፋት 454.3 ኪ. ሜ2 ሲሆን የሕዝብ ሥርጭት/አሰፋፈር/ ከቦታ ቦታ የሚለያይ ሲሆን ጥግግቱ በስኩየር ኪ.ሜትር 106 ሰው ነው፡

